Core Values

core calue....

ኮር እሴቶቻችን 

የእግዚአብሔር መንግስት የሕይወት ዘይቤ 

እያንዳንዱ አባል በእግዚአብሔር ቃል እንደተገለጸው የእግዚአብሔርን መንግስት እሴቶች በሙላት በሚያንጸባርቅ የሕይወት ዘይቤ ለመኖር የተሰጠ መሆን ይገባዋል። ሰዎች እውነትን በማወቃቸው ብቻ የሚረኩ ሳይሆኑ: ነገር ግን ያወቁትን እውነት የሚያደርጉ መሆን ይገባቸዋል።

የግል ሂደት

የእግዚኣብሔርን መንግስት እሴቶች በሕይወት ለመግለጽ: ከግል ባህሪና ከባህላዊ የአስተሳሰብ ጠባብነት ነጻ መውጣት ይጠይቃል። እያንዳንዱ አባል ስለ ግል ማንነት፣ የግል ፍላጎትና ምኞት: ቀጣይነት ባለው የመሞት ሂደት ውስጥ ለማለፍ የተሰጠ መሆን አለበት። ይህም ወደ መሆን ሊመጣ የሚችለው በሕይወታችን ውስጥ የሚገኙትን የኃጢያት ዘሮች ለይቶ በማወቅና በለውጥ ሂደት ውስጥ ለማለፍ ኃላፊነት በመውሰድ ነው።

አምልኮ፣ ጸሎትና የእግዚአብሔርን ቃል ማጥናት

አምልኮ ጸሎትና የእግዚአብሔርን ቃል ማጥናት ለእግዚአብሔር መንግስት የሕይወት ዘይቤ ቁልፍ ነገሮች ናቸው። አምልኮ እግዚአብሔር በመካከላችን ከፍ እንዲልና እንዲነግስ ያደርጋል፤ እንዲሁም የጉባኤውን መንፈሳዊ ሁኔታና ባህርያት ይቀርጻል።

የጋራ ጸሎታችን በባህርዩ መንግስታዊ ሲሆን፤ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ፈቃድ በምድር ላይ ለማወጅና ወደፊት ለመግፋት ዋነኛ መንገድ ነው። በተጨማሪም የእግዚአብሔር መንግስት ወደፊት እንዲገሰግስ የሚያደርግ አስፈላጊ መሳሪያ ነው።

ምንም እንኳን ዘመናዊ ብንሆንም ጥንታውያን ሕዝብ ነን። በዓለም አሰራር ውስጥ በሚገኙ ምድራዊ መዋቅሮች ውስጥ ለመስራት ብቃት ያለንና፤ በምድር ላይ የሰውን ሕይወት ከሚቀርጹት የሶሻል፣ የፖለቲካና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ጋር የተገናኘንና: ስለነዚህ ሙሉ መረዳት ያለን ብንሆንም እንኳን: በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የጸኑትን እና የማይለወጡትን መርሆችንና መሰረታዊ እምነትን ሙሉ በሙሉ የራሳችን ያደርግን ሕዝብ ነን። ይህም አቋማችን በግል ጸሎታችን፣ ቃሉን ለማጥናት ባለን ጠንካራ ፍላጎትና: በአኗኗር ዘይቤአችን ይንጸባረቃል።

ጉዞ

በቤተክርስቲያን አገልግሎት ዙሪያ ከተገነባ ሃይማኖታዊ አሰራር በመለያየት: ወደ ዘላለማዊውና ወደፊት እያደገ በሚሄደው የእግዚአብሔር ዓላማ እውነታ ውስጥ ገብተናል። በዚህ ይዘት ውስጥ በእግዚአብሔር ላቅ ወዳለ ትክክለኛ አቋም የሚደረገው ጉዞ፣ ሽግግርና እንቅስቃሴ የአባሎቻችንን ሕይወትና አመለካከት ይወስናል።

አገልጋይነት 

በተፈጥሮአችን ለመገልገል ሳይሆን ለማገልገል እንደተሰራን እንገነዘባለን። ይህ በክርስቶስ ሕይወት ውስጥ እንደነበረ እንደዚሁም የእያንዳንዱ የኬኤልሲ አባላት የባህሪ መገለጫ መሆን አለበት። እንዲሁም ዓለማቀፉን የእግዚአብሔር መንግስት ማሕበረሰብ እንደሚያገለግል ቤተክርስቲያን: ይህ ቁልፍ እሴታችን ነው።

የጋራ ሕይወት 

የአብ፣ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ስብእና በአንድነት አንድ እግዚአብሔርን ያሳያል። በእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ የተፈጠርን እኛም: የእርሱን ማንነት መግለጽ ይጠበቅብናል። ይህንን መረዳታችን እርስ በርስ ያለንን ግንኙነትና ማሕበረሰባችንን የምንገነባበትን መንገድ ይወስናል። እድገት ደግሞ የሚመጣው እያንዳንዱ ክፍል ለሌላው ክፍልና ለአጠቃላዩ አካል ጥቅም በሚያደርገው የፍቅር አስተዋጽኦ፣ በአንድነት በመያያዝና ተሳታፊ በመሆን ውስጥ ነው። የጋራ ሕይወት (Shared Life) በኬኤልሲ ውስጥ ብቻ የሚታይ እውነታ ሳይሆን፡ ከሰፊው ዓለማቀፍ የእግዚአብሔር መንግስት ማሕበረሰብ ጋር ባለን ግንኙነት ውስጥም ልቆ የሚታይ ነው።

ዓለማቀፋዊነት 

ኬኤልሲ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ዲያስፖራ ባሉበት ቤተክርስቲያን ሁሉ ተሃድሶንና የመዋቅር ለውጥን ለማምጣት: እንዲሁም በ21ኛው ክፍለ ዘመን ስለ እግዚአብሔር መንግስት መስፋት በምድር ላይ ለሚገኙ ሕዝቦች ሁሉ በድፍረትና በአዲስ መልኩ ለማወጅ ተልእኮ አለው።

ስለዚህም በድርጊታችን ወይም በአመለካከታችን ጠባቦች መሆን አንችልም። እያንዳንዱ አባል በዚህ ዓለማቀፍ ተልእኮ ውስጥ: በምድር ላይ በሚገኙ ሕዝቦች ላይ ጠንካራ መንግስታዊ አዋጆችን በማወጅ፣ ዋጋ በመክፈል በማገልገልና፣ ከአለም አቀፉ የእግዚአብሔር መንግስት እውነታ ጋር አብሮ በሚሄድ አመለካከት በመለወጥ ተሳታፊ መሆን ይጠበቅበታል።

እግዚአብሔር በዓለም ዙሪያ ልዩ የሆነና ተጽእኖ የሚያመጣ አንድ ሕዝብ እየቀረጸ ነው። ዓለማቀፋዊነታችን እየጨመረ በሄደ ቁጥር: የእግዚአብሔርን መንግስት በሚቃወሙ አሰራሮች ላይ ውድቀት የሚያስከትሉና: የእግዚአብሔር መንግስት በምድር ዙሪያ በሚገኙ ሕዛቦች መካከል እንዲሰፋ የሚጠቅሙ አቅራቦቶች እንዲለቀቁ አስተዋጽኦ ያደርጋል።