Leadership

የኬኤልሲ አመራር

ኬኤልሲ ራሱን የቻለ አንድ ድንበር የለሽ አለም አቀፍ የእግዚአብሔር መንግስት ማሕበረሰብ ሲሆን: አመራሩና ማሕበረሰቡ ከኮንግረስ ደብሊውቢኤን መስራችና ዋና መሪ ከሆነው ከዶር ኖኤል ውድሮፍ ጋር በትክክል በመያያዝ (ኮኔክት በመሆን) በአንድ ሐዋርያዊ ጥላ ስር የሚኖር ቤተክርስቲያን ነው።

የኬኤልሲ አመራር መዋቅር – የመጀመሪያው የአመራር ደረጃ ዋና መሪዎች ወይም ኤልደርሺፕ የምንለው ሲሆን ቀጥሎ ያለውን ሁለተኛ መሪዎች ብለን እንጠራዋለን።

CLC

Eldership

esayas tilahun_

ኢሳያስ ጥላሁን

ኢሳያስ ጥላሁን የኪንግደም ላይፍ ሴንተር ዋና መሪ (ሴኒየር ኤልደር) ሆኖ እያገለገለ ይገኛል:: ኢሳያስ ከእግዚአብሔር ከተቀበለው ተልእኮ የተነሳ መሰረቱን በስዊዘርላንድ ባደረገው የኬኤልሲ-ሃብ (KLC-Hub) እንዲሁም በኖርዌይ፣ በእንግሊዝ፣ በካናዳ፣ በጣሊያን፣ በአውስትራሊያና በሌሎችም አገሮች በሚገኝ የኬኤልሲ አካል በዋና መሪነት ያገለግላል። በተጨማሪም በስዊዝ የኮንግረስ ሴክተር የሆነው የKCN አስተባባሪ (Coordinator) ሲሆን፤ በኢትዮጵያውያንና ኤርትራዊያን የኮንግረስ ኮኦርዲኔተርስ ቲምም EECCT (Ethiopians & Eritreans Congress Coordinators Team) አባል ነው። ይህ ቲም ኃላፊነቱ በኢትዮጵያና በኤርትራ ውስጥ እንዲሁም በዲያስፖራው መካከል የC-WBNን እንቅስቃሴዎችን በኃላፊነት ማካሄድ ነው። ኢሳያስ ጥላሁን ባለትዳር ሲሆን ከባለቤቱ ከፌቨን ሓደገ ጋር ከ17 ዓመታት በላይ በስዊዘርላንድ በሉዘርን ከተማ ነዋሪዎች ናቸው።

kebedom Gmariam

ከበዶም ገብረማርያም

ከበዶም ገብረማርያም በኪንግደም ላይፍ ሴንተር ምክትል መሪነት (አሶሼት ኤልደር) በመሆን እያገለገለ ይገኛል:: ከዚህ በተጨማሪ በኢትዮጵያውያንና ኤርትራዊያን የኮንግረስ ኮኦርዲኔተርስ ቲም EECCT (Ethiopians & Eritreans Congress Coordinators Team) አባል ነው። ከበዶም በስዊዝ ፌደራል ትሬይን ካምፓኒ ውስጥ በቴሌኮሚኒኬሽን ዴፓርትመንት ውስጥ በኢንጂነርነት ሞያ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል:: ከበዶም ባለትዳር ሲሆን ከባለቤቱ ኒጊ ብርሃነ አብርሃና ከሦስት ልጆቻቸው /ናኦሚ፣ ዴቦራ እና አቢጋኤል/ ጋር በሎዛን ከተማ ከ25 ዓመታት በላይ ነዋሪዎች ናቸው።

የሁለተኛ መሪዎች | Secondary Leadership

የሁለተኛ መሪዎች ቲም በኮሚኒቲው ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ቲሞችን (teams) ኮኦርዲኔት የሚያደርጉ እና በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ የሚገኙ እስከ 30 የሚደርሱ ወንዶች እና ሴቶች መሪዎች ይገኙበታል::