About us

ኬኤልሲ | ድንበር የለሽ አለም አቀፍ የእግዚአብሔር መንግስት ማሕበረሰብ

ኬኤልሲ የወቅቱ የእግዚአብሔር እውነት የሆነውን ሐዋሪያዊ ተሃድሶን ማወጅና እንዲገሰግስ ማድረግ ተልእኮአቸው ያደረጉ: በእግዚአብሔር መንግስት መርሆችና እሴቶች የተገነቡ: በዋነኛነት ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን የሚገኙበት ድንበር የለሽ ዓለም አቀፍ የእግዚአብሔር መንግስት ማሕበረሰብ (ቤተክርስቲያን) ነው። ይህ ማሕበረሰብ በስዊዘርላንድ ውስጥ በሉዘርን፣ ሎዛን፣ በርን፣ ዙሪክ እና ባዝል በሚባሉ ዋና ዋና ከተሞች እንዲሁም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ይገኛል:: ኬኤልሲ የኮንግረስ ደብሊውቢኤን አለም አቀፍ የሐዋሪያዊ አሰራር አካል ነው።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ተመልሶ እስኪመጣና ከእርሱ ጋር ፊት ለፊት እስክንተያይ ድረስ፡ በዚህ ሟች በሆነው ሰውነት ውስጥ ሆነን በዘላለማዊ ሕይወት ኃይል እና ስልጣን በእምነትና በድል አድራጊነት መኖር ከጌታ የተቀበልነው አዲስ ሕይወት ነው። ስለዚህም ተልዕኮአችን ከሰይጣን እና ከሰው አሰራር ተቃውሞ ባሻገር: የእግዚአብሔርን መንግስት የሕይወት ዘይቤ በትክክለኛ መንገድ በወንዶች፣ በሴቶች፣ በወጣቶች፣ በቤተሰቦች እና በልጆች: በአጠቃላይ የሕይወት ክፍል ላይ ገንብተን የእግዚአብሔር መንግስት የሕይወት ማእከል መሆን ነው።

እግዚአብሔር ማን እንደሆነ፣ ባህሪው ምን እንደሚመስል እንዲሁም የእግዚአብሔር ቃል ህያውና የሚሰራ መሆኑን ለመግለጽ እውቀትና ድፍረት በጠፋበት በዚህ ዘመን: ትኩረታችንን በቀዳሚነት ሕይወታችንን መገንባት ላይ በማድረግ እግዚአብሔር ህያው እንደሆነ በሕይወታችን እናሳያለን። በዚህም ሰዎች ሕይወታችንን ተመልክተው፡ እግዚአብሔር አሁንም እየሰራ እንዳለና: ለሕይወታቸው፣ ለትዳራቸው እና ለልጆቻቸው ዓላማ እና እቅድ እንዳለው እንዲያዩና በማድረግ: በሰዎች ላይ ተስፋ እና እምነት በመፍጠር ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር እናቀርባለን።

 ቀዳሚ ዓላማዎች

በእግዚአብሔር መርህና እሴቶች የተገነባ: ተግባራዊ እና ሞዴል የሆነ ጠንካራ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አመራር ያለው ኮር የሆነ ሐዋሪያዊ የእግዚአብሔር መንግስት ማሕበረሰብ መገንባት:

ሐዋርያዊ ተሃድሶን ወደ ቤተክርስቲያን በማምጣት በተሃድሶ ውስጥ ባለው የክርስቶስ ቅባትና ጥበብ አማካኝነት ቤተክርስቲያንን እንደገና ለክርስቶስ ኢየሱስ የምትመች አድርጎ ማዋቀር እና ለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት መንገድ መጥረግ

የቤተክርስቲያን መሰረታዊ ቅባት የሆኑትን ሐዋርያትና ነቢያት ከሌሎቹ የአምስቱ የክርስቶስ አገልግሎቶች ክፍል ከሆኑት ወንጌላውያን እረኞች እና አስተማሪዎች ጋር በመቀበል ቤተክርስቲያን በጠንካራ መሰረት ላይ እንድትመሰረት ማድረግ – ይህም ቤተርክስቲያን ጥንካሬና ብስለት እንዲኖራት ያደርጋታል::

የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም፣ ማንነት፣ ባህሪውን እና ቃሉን በተግባር በመካከላችን ባለን አሰራር ሁሉ ውስጥ ከፍ ማድረግ ትልቁ ትኩረታችን ነው። በፍጥረት ሁሉ ላይ አዳኝነቱንና ጌትነቱን በማወጅ እርሱ የላከንን ስራ መስራትና መፈጸም ዋናው አላማችን ነው

ትንቢታዊ አገልግሎት፣ መለኮታዊ ፈውስ፣ ተአምራትና ሁሉም የጸጋ ስጦታዎች: የክርስቶስን ማንነትና ባህሪ በሚያንጸባርቅ መልኩ  የሚገለጡበት የእግዚአብሔር መንግስት ማሕበረሰብ/ቤተክርስቲያን መሆን

የእግዚአብሔር ቃል አሁንም በሰዎች ባህሪ፣ ስሜት፣ ነፍስ እና አስተሳሰብ ላይ ተጽዕኖ በማምጣት: የግል እና የጋራ ሕይወትን የሚያሳድግ እንዲሁም እግዚአብሔር የሚፈልገውን ዓይነት ሰው እና ማሕበረሰብ ማፍራት የሚያስችል ኃይልና ብቃት እንዳለው በቃልም በተግባርም መግለጽ

ኬኤልሲ ውስጥ ያሉ ቅዱሳን: እግዚአብሔር በውስጣቸው ያስቀመጠውን ብቃት እና መለኮታዊ ጥሪ ወደሚያስፈጽሙበት ስፍራ እንዲመጡ በእግዚአብሔር ሃሳብ ማስታጠቅና መርዳት

  • ይህንን ተልዕኮ ለማስፈጸም በቀዳሚነት – ከፍተኛ  ትኩረት የሰጠነው:-
    • እግዚአብሔር የሰጣቸውን መለኮታዊ የመሪነት ስፍራቸውን በመያዝ ቤተሰባቸውን የሚመሩና የሚያስተዳድሩ ጠንካራ ወንዶች መገንባት
    • በመንፈሳዊ ሕይወታቸው የበሰሉና በስልጣን ስር መሆን የተማሩ ጠንካራ ሴቶች መገንባት
    • በእግዚአብሔር ነገር የተያዙ፣ መንፈሳዊ የሆኑ፣ በዚህ ምድር ላይ እንዴት መኖር እንዳለባቸው የተረዱና ሙሉ ብቃት ያላቸው ጠንካራ ወጣቶች እና በጥበብ የተሞሉ ልጆች ማፍራት
    •  በእግዚአብሔር መርህና እሴት የተገነባ ጠንካራ ቤተሰብ መገንባት

[/vc_column_text][/vc_column][/vc_row]

በተጨማሪም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያሉትን ቤተክርስቲያናት ከመረዳትና ከፈቃደኝነት በመነጨ የልብ ለልብ መያያዝ፣ በቃል ኪዳን በመተሳሰርና አንድ በመሆን የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ እቅድ በምድር ላይ ማስፈጸም እንዲችሉ: በሐዋርያዊ የመረብ አሰራር እንዲያያዙ ማድረግ ሕዝ 32፡3-4::

ለዚህም የመረብ አሰራር: ኬኤልሲ ጠንካራ መሰረት/Strong Base፣ ኮር/Core፣ በር/Portal፣ የእርቅ ቦታ/Place of Reconcilation፣ የማመሳከሪያ ቦታ/Place of Reference፣ የአቅርቦት ቦታ/ Place of Resource፣ የመርህና የእሴት ቦታ /Place of Principles & Values እንዲሁም የመጠለያ ቦታ/ Place of Sanctuary መሆን ከእግዚአብሔር የተቀበልነው ተልእኮ ነው።

IMG_5150-2

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት እርሱ የፍጥረት ሁሉ ጌታ ነው። ተመልሶም ይመጣል: እኛም ከእርሱ ጋር ለዘላለም አብረን እንኖራለን። አሜን!